እንደሚታወቀው የማስልጠኛ ተቋማችን በኢትዮጵያ “የመጀመሪያው የግል አሽከርካሪወች ማሰልጠኛ ተቋም እና ፋና ወጊ” በመሆን ሕጋዊ ዕውቅና አግኝቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረው በ1993 ዓ.ም. ነው። በተያያዘ አሰራር “የመማሪያ እና ተጓዳኝ መጻህፍቶችን” በማዘጋጀት ለደንበኞች ተደራሽ ለማድረግም ቀዳሚወችነን። “የመንገድ ላይ ትራፊክ አደጋን አስከፊነት” አስመልክቶ በአገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚዘጋጁ የተለያዩ መድረኮች ላይም በመሳተፍ ዘርፈብዙ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንገኛለን።
ወደ ሴፍቲ የአሽከርካሪዎች ት/ቤት እንኳን ደህና መጣችሁ!
ተምረው፤ ይንዱ!
50,000
ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ!
ሰልጣኝ አሽከርካሪዎች
50+
ሰራተኞች
የዋና ሥራ-አሥኪያጅ እና መሥራች መልዕክት
ደበበ ጤናው
ዋና ሥራ-አስኪያጅ
የተከበራችሁ የድርጅታችን ደንበኞች፣አጋሮች እና ባለድርሻ አካላት!
እንደሚታወቀው የማስልጠኛ ተቋማችን በኢትዮጵያ “የመጀመሪያው የግል አሽከርካሪወች ማሰልጠኛ ተቋም እና ፋና ወጊ” በመሆን ሕጋዊ ዕውቅና አግኝቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረው በ1993 ዓ.ም. ነው። በተያያዘ አሰራር “የመማሪያ እና ተጓዳኝ መጻህፍቶችን” በማዘጋጀት ለደንበኞች ተደራሽ ለማድረግም ቀዳሚወችነን። “የመንገድ ላይ ትራፊክ አደጋን አስከፊነት” አስመልክቶ በአገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚዘጋጁ የተለያዩ መድረኮች ላይም በመሳተፍ ዘርፈብዙ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንገኛለን።
የአገልግሎት አሰጣጥን በየጊዜው የማሻሻሉ ጉዳይ ግንባር ቀደም ሀላፊነት እንደመሆኑ፤ የተሻሻለውን “የድህረገፅ አገልግሎት” ይዘን ቀርበናል። “በአዲሱ ድህረገፃችን” ደንበኞችን ማዕከል ባደረገ መልኩ መሠረታዊ መረጃወችን ለማካተት ጥረት አድርገናል። በምትሰጡት አስተያየት መሠረትም ይበልጥ አካታች እንዲሆን በማስቻል የምናዳብረው ይሆናል።
ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ በመቶሽወች ለሚቆጠሩ ደንበኞች አገልግሎት መስጠት የቻልነው ከእናንተ ከደንበኞቻችን እና አጋሮቻችን በአገኘነው “አመኔታ እና ተመራጭነት” በመሆኑ፤ልባዊ ምሥጋናችንን እናቀርባለን!
በመጨረሻም የድርጅታችን መሪ ቃል “ተምረው-ይንዱ፤ቅድሚያ ለደህንነት!” [Learn & Drive: Safety First] የሚል እንደመሆኑ፤ ለተግባራዊነቱ ሁላችንም በተናጠልም ሆነ በቅንጅት የምናደርገውን የዘወትር ጥረት ችላ እንዳንል ከአደራ ጭምር አሳስባለሁ!
ተመራጭ የሆንባቸው ልዩ ዕድሎች!
ደንበኞችን ማዕከል ያደረገና ያስቀደመ አገልግሎት!
የረጅም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው ባለሙያወች መኖር!
የአማራጭ ማሰልጠኛ አካባቢወች (ቅርንጫፎች) መኖር!
የተሀድሶ ሥልጠና
በቴክኖሎጅ የታገዙ አገልግሎቶች!
ለምርምርና ከሂደቶች ለመማር የምንሰጠው ትኩረት!
የሥልጠና አማራጮች
መደበኛ ሥልጠና (የንድፈሀሳብና የተግባር)
ለሞተር፦
- ለንድፈሃሳብ 41:00 ስዓት
- ለወርክሾፕ 7:00 ስዓት
- ለተግባር 15:00 ስዓት
ለአውቶሞቢል
- ለንድፈሃሳብ 53:00 ስዓት
- ለወርክሾፕ 8:00 ስዓት
- ለተግባር 20:00 ስዓት
ለሕዝብ አንድ፦
- ለንድፈሃሳብ 57:00 ስዓት
- ለወርክሾፕ 8:00 ስዓት
- ለተግባር 35:00 ስዓት
በደንበኞች ፍላጎት የሚዘጋጁ ልዩ ሥልጠናወች
- አደጋን ተከላክሎ ማሽከርከር፦ ከ 8:00 እስከ 24:00 ወይም ከ 1ቀን እስከ 3ቀን
የሥልጠና ማዕከላት
የተወሰኑ ደንበኞቻችን እና አጋሮቻችን ዝርዝር








