የምስክር ወረቀቶች እና ሽልማቶች ባለፉት 24 አመታት የአገልግሎት ዘመን ላበረከትናቸው ተጨባጭ ውጤቶች “ከግለሰቦች፣ ከመንግሥታዊ አካላት፣መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እና ከንግድ ድርጅቶች”፤ የተለያዩ “የዕውቅና ሰርትፊኬቶችን እና ሽልማቶችን” አግኝተናል። በተመሳሳይ ሁኔታ ድርጅታችንም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ሰራተኞቻችን እና አጋሮቻችን ልዩ ልዩ የዕውቅና ሰርትፊኬቶችን እና ሽልማቶችን ሰጥቷል። ከዚህ አኳያ በየአመቱ “የድርጅታችን ሰራተኞች እና አጋሮች ቀን“ በሚል የምናከብረው ፕሮግራም ተጠቃሽ ነው።